እነ እስክንድር ነጋ የተጠሩት ጉባኤ ተከለከለ

0
223

ፓርቲ ለመመስረት በማሰብ ቅድመ ፓርቲ ምስረታ ጉባኤ ለማድረግ ባልደራሱ የጠራው ጉባኤ እንዳይካሔድ ተከለከለ፡፡

አቶ እስክንድር ነጋ እንዳስታወቀው ለኢንተር ኮንቲኔታል ሆቴል 90 ሺ ብር የአዳራሽ እና የአቅረቦት ክፍያ የከፈሉ እና ያሟሉ ቢሆንም ከበላይ አካል ትዕዛዝ መጥቶልናል በሚል ሆቴሉ ጉባኤውን ከልክሏል፡፡

ሆቴሉ ሙሉ በሙሉ በሩን በካቦ ገመድ እንዲቆለፍ እንዳደረገም ነው የታወቀው፡፡

እነ እስክንድር ነጋ ቅድመ ፓርቲ ምስረታ ጉባኤ ለማካድ የተለዩ የተቋማት ሀላፊዎችንና የሚዲያ ተቋማትን ጋብዘው የነበረ ሲሆን ጉባኤው ግን መካሔድ አልቻለም!
ልደራሱ ተብሎ የሚጠራው ስብስብ ወደ ፖለቲካ ፓርቲነት እንደሚያሳድግ ያሳወቀው ባሳለፍነው ሳምንት ነበር፡፡

አውሎ ሚዲያ ጥር 3/2012 ዓም

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ