አራት የአማራ ክልል ተወላጅ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በኦሮሚያ ባልታወቁ ሀይሎች መጠለፋቸውን አቶ ተመስገን ጥሩነህ ተናገሩ፡፡

0
342

የአማራ ክልል ርዐሰ መስተዳድር በኦሮሚያ ክልል ባሉ ዩኒቨርሲቲዎች የተመደቡ እና ወደ ቤተሰቦቻቸው ለመመለስ በጉዞ ላይ የነበሩ 4 የአማራ ክልል ተወላጆች ባልታወቁ ሰዎች ከታገቱ ሰንበትበት ብሏል ሲሉ ዛሬ ተናግረዋል፡፡
ፕሬዚዳንቱ ዛሬ በሰጡት መግለጫ ተማሪዎቹ የታገቱ መሆናቸው ለፌደራል ፖሊስ እና ለመከላከያ ሐይል ብናሳውቅም እስካሁን ምን መረጃ መገኘት አልቻለም ሲሉ መናገራቸውን አማራ ቴሌቪዥን ዘግቧል፡

አቶ ተመስገን ጥሩነህ የተማሪዎችን ጉዳይ እየተከታተልን ነው ያሉ ሲሆን ውጤቱን በቅርብ ለህዝብ እናሳውቃለን ብለዋል፡፡

በአርማጭሆ 6 ህፃናትን አግተው የገደሉ 50 ተጠርጣሪዎችም ተይዘዋል ብለዋል፡፡

በተጨማሪም በሞጣ መስጅድ ያቃጠሉ እና በጉዳዩ ላይ ያሉ በርካታ ተጠርጣሪዎችም በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተካሔደ ነው ማለታቸው ተሰምቷል፡፡

አውሎ ሚዲያ ታህሳስ 27/2012 ዓ .ም

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ