በዩኒቨርሲቲዎች በ440 ታመሪዎች ላይ ህጋዊ እርማ እንዲወሰድ አድርግያለሁ ብሏል የሳይንስ ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ፡፡

0
113

በመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በተከሰቱ ግጭቶች ውስጥ ተሳትፈዋል በተባሉ 440 ተማሪዎች ላይ ህጋዊና አስተዳደራዊ እርምጃ መውሰዱን የሳይንስ ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ።

ሚኒስቴሩ ከፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ጋር በመሆን በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እያጋጠሙ ያሉትን ችግሮች ለመፍታት አየተከናወኑ ባሉ ስራዎችና ቀጣይ እርምጃዎች ላይ መግለጫ ሰጥቷል።

እርምጃው ከማስጠንቀቂያ ጀምሮ ከትምህርት ገበታቸው እሰከማገድ የሚደርስ ቅጣት መሆኑም ተመልክቷል።
በዚህ መሰረት እርምጃ ከተወሰደባቸው ተማሪዎች ውሰጥ ከ170 በላይ የሚሆኑት የአንድ ዓመት እገዳና ሙሉ በሙሉ ከተቋማቱ ማባረርን ያካትታል።

ከ270 በላይ ተማሪዎች ደግሞ የመጨረሻ ማስጠንቀቅያ እንደተሰጣቸው ሚኒስትር ዴኤታው ዶክተር ሳሙሄል ክፍሌ ተናግረዋል።

ኢዜአ እንደዘገበው ከዚህም በተጨማሪ በ10 መምህራንና የአስተዳደር ሰራተኞች ላይም እርምጃ መወሰዱን ጠቁመዋል።
ባለፈው ጥቅምት ወር በወልዲያ ዩኒቨርስቲ በተማሪዎች መካከል በተከሰተ ግጭት የተማሪዎች መሞትን ተከትሎ በሌሎች የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች አለመረጋጋቶች እየተስተዋሉ መሆኑ ይነገራል።

አውሎ ሚድያ ታህሳስ 27/2012 ዓ/ም

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ