ሳልሳይ ወያነ ትግራይ (ሳወት) አቶ ሃያሉ ጎዶፋይን የፓርቲው ሊቀመንብር አድርጎ መረጠ፡፡

0
220

“የትግራይ ጥቅም መሰረቱ ትግራይ ባደረገው ሁለንተናዊ ትግል ይረጋገጣል” በሚል መሪ ሃሳብ ለሁለት ተከታታይ ቀናት ሲካሄድ የቆየው የሳልሳይ ወያነ ትግራይበ (ሳወት) የመጀመርያ ጉባኤ የተለያዩ ሃላፊነትና ሹመት በማፅደቅ ተጠናቋል።

ፓርቲው ዛሬ በሰጠው መግለጫ እንዳሳወቀው በጉባኤውም የተለያዩ የሕብረተሰ ክፍሎች ፣ የፓርቲ ተወካዮች በተለይም ትግራይ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ ፓርቲዎች ፣የምርጫ ቦርድ ፅ/ቤት ተወካይ ፣የሃይማኖት መሪዎች ፣የሲቪክ ማህበራት ፣የሞያ ማህበራት ፣ የዩኒቨርሲቲ ተወካዮች ተገኝተዋል፡፡

ጉባኤው ታህሳስ 25/2012 ዓ/ም ከሰአት በኋላ 3 ፕሬዚድየም አባላትን በመምረት በ7 ቡድን በመቧደን ሰፊ ውይይትና ክርክር በማድረግ የፓርቲው ፕሮግራም ማፅቅ ተችሏል ተብሏል፡፡
ጉባኤው በቀጣይ ቀን ማለትም ታህሳስ በ26/2012ዓም ከሰአት በኋላ የፓርቲው ብሄራዊ አመራር (ማእከላዊ ኮሚቴ) መርጧል።

በዚህም መሰረት በ3 የምርጫ አስፈፃሚዎች እየተመራ 2 ሴቶች ን ያካታተ 25 ብሄራዊ አማራር፤ 1 ሴት የተካታተችበት 5 የቁጥጥር ኮሚሽን አባላት በመምረጥ ተጠናቋል፡፡

ማእከላዊ ኮሚቴው ድርጅቱ በሰጠው ስልጣን መሰረት የፓርቲው ሊቀ-መንበር አቶ ሃያሉ ጎዶፋይ እና ምክትል ሊቀመንበር ደግሞ አቶ አሉላ ሃይሉን የመ፣ረጠ ሲሆን የተለያዩ ተጨማሪ ሃለፊዎችንም በየዘርፉ ሰይሟል፡፡

አዉሎ ሚድያ ታህሳስ 27/2012ዓ/ም

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ