የኢራን አብዮታዊ ጥበቃ ኃይል አዛዥ ጀነራል ቃሲም ሶሌኢማኒ በኢራቅ በአሜሪካ ወታደሮች ተገደሉ፡፡

0
63

ጀነራል ቃሲም የተገደሉት በኢራቅ ዋና ከተማ ባግዳድ ኤር ፖርት አቅራቢያ በመኪና ሲንቀሳቀሱ በነበሩበት ወቅት ነው ተብሏል፡፡
ጀነራል ቃሲም ሶሌኢማኒ በመካከለኛው ምስራቅ ሃገራት ውስጥ ተፅዕኖ ፈጣሪ ከሚባሉ ግለሰቦች መካከል አንዱ እንደነበሩ ይነገራል።

የአሜሪካ የመከላከያ ዋና መሥሪያ ቤት ፔንታጎን ጀነራል “ሶሌኢማኒ የተገደሉት በፕሬዝደን ዶናልድ ትራምፕ ትዕዛዝ ነው” ብሏል።
የኢራን ዋና መሪ አያቶላህ አሊ ጥቃቱን በተመለከተ በሰጡት መግለጫ “ወንጀለኞቹ ከባድ የበቀል እርምጃ ይጠብቃቸዋል” ብለዋል ፡፡
ለሶስት ቀናትም ብሄራዊ የሀዘን ቀን ታውጇል ነው የተባለው።
ጀነራሉ የተገደሉት በኢራቅ ባሉ የአሜሪካ ወታደሮች ላይ ጥቃት ለመፈጽም አቅደዋል በሚል መሆኑን አሜሪካ አሳውቃለች፡፡
የጀነራሉ መገደል በአሜሪካ እና ኢራን መካከል ያለውን ውጥረት እንዳያባብስ ስጋት ፈጥሯል፡፡

አውሎ ሚዲያ ታህሳስ 24/2012 ዓም

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ