ኢትዮጵያ በአሁኑ ሰአት የፈቀደችው ከፍተኛ የውጭ ሃይሎች ጣልቃገብነት በቀጣይ ከፍተኛ ችግር ያመጣል ሲሉ አቶ ልደቱ አያልው ተናገሩ፡፡

0
101

አቶ ልድቱ አያሌው በዚህ ወቅት በኢትዮጵያ በከፍተኛ ደረጃ የውጭ ሃይሎች ጣልቃ ገብነት አለ ሲሉ ተናገረዋል፡፡

በተለይም በዚህ ሽግግር ወቅት ያለው ጣልቃ ገብነት የሰፋ ከመሆኑም በላይ የተጠና
እና በግልፅ ያልታወቀ በመሆኑ አሳሳቢ ነው ብለዋል አቶ ልደቱ፡፡

ከአውሎ ሚዲያ ጋር ቆይታ ያደረጉት ፖለቲከኛው አቶ ልደቱ አሁን ላለው የሀገሪቱ ሁኔታም ሆነ ለአዲሱ ትውልድ አሁን ያለው የውጭ ሃይል ጣልቃ ገብነት ከፍተኛ ችግርን የሚያስከትል ነው ብለዋል፡፡

በኢትዮጵያ የለውጥ ሂድት ውስጥ በታሪክም የተለያዩ ሃይሎች ጣልቃገብነት የነበረ ቢሆንም በዚህ ወቀት ያለው ግን ሰፊና አደገኛ ነው ሲሉ አክለው ተናገረዋል፡፡

በቀጣናው ያለውን ሁለንተናዊ የፖለቲካ ሁኔታ ያልተረዳው የለውጥ ሃይሉ ከፍተኛ ጣልቃ ገብነትን በመፍቀዱ ምክንያት ወደ አልተፈለገ ችግር ውስጥ ሊያስጋብን እና የውስጥ ሃይል መፈረካከስን ሊያሰፋው ይችላል ብለዋል፡፡

አቶ ልደቱ የውሥጥ ችግሮቻችንን መፍታት አለመቻላችን እና በአንድነት አለመቆማችን ለውጭ ሃይሎች ከፍተኛ እድል ፈጥሯል ብለዋል፡፡

አውሎ ሚዲያ ታህሳስ 24/2012ዓ. ም

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ