በወላይታ ዞን ባይራ ኮይሻ ወረዳ ሁለት ህጻናት በጅብ መበላታቸውን የወረዳው ፖሊስ አስታወቀ።

0
181

የወረደው ፖሊስ አዛዥ ኢንስፔክተር ደስታ ዳና ዛሬ ለኢዜአ እንደገለጹት በትናንትናው ዕለት ህጻናቱ በጅብ ተበልተው ህይወታቸው ያለፈው በወረዳው ቃናፋ ጎደራ በሚባል የገጠር ቀበሌ ነው።
ከምሽቱ 1፡00 አካባቢ ከዱር ድንገት በመጣ ጅብ የተበሉት ህጻናት የ8 እና የ11 ዓመት ዕድሜ ያላቸው ህጻናት ናቸው።
እንደ ኢኒስፔክተር ደስታ ገለጻ የስምንት ዓመቷ ህጻን ከቤቷ ደጃፍ ላይ እንዳለች በጅቡ ድንገት የተወሰደች ሲሆን የ11 ዓመቱ ህጻንም ኳስ ተጫውቶ ወደ ቤቱ ሲመለስ በጅብ ተበልቶ ሕይወቱ አልፏል።
ጅብ በቀጣይም ወደአካባቢው መጥቶ ተጨማሪ ጉዳት እንዳያደርስ ከቀበሌው በቅርብ ርቀት ላይ የሚገኙ የጅብ ጉድጓዶችን የመድፈን ስራ ህብረተሰቡን በማስተባበር መሰራቱን ኢኒስፔክተር ደስታ አስታውቀዋል።

በወረዳው በጅብ የሚደርስ ጉዳት ብዙም አለመለመዱን ገልጸው በአሁኑ ወቅት የአካባቢው ማህበረሰብ ከጸጥታ ኃይሎች ጋር በመሆን ጅብ ይኖርባቸዋል በተባሉ አካባቢዎች የማሰስ ሥራ እየሰራ መሆኑን አመልክተዋል።
እንደ ኢዜአ ዘገባ በወላይታ ዞን ሶዶ ዙሪያ ወረዳ ከአንድ ወር በፊት ሦስት ህጻናት በጅብ መበላታቸው ይታወሳል።

አውሎ ሚዲያ ታህሳስ 23/2012 ዓም

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ