በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ግጭት እንዳይከሰት በሚደረገው ጥረት የክልልና የከተማ አስተዳደሮች ሥራ በቂ አይደለም ተባለ።

0
65

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ምክር ቤት ጉባኤ የ45ቱም ዪንቨርሲቲ ፕሬዝዳንቶች በተገኙበት በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው።ጉባኤው በዩንቨርሲቲዎች ሠላም፡በምርምር ፡መማር ማስተማር እና ቴክኖሎጂ ላይ እንደሚያተኩርም ተገልጿል።

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ሂሩት ወልደማርያም በዚህ ጊዜ እንደተናገሩት በትምህርት ተቋማቱ የሚስተዋለውን አለመረረጋት ለመፍታት በሚደረገው ርብርብ የክልሎች እና የከተማ አስተዳደሮች ድጋፍ በቂ አይደለም ብለዋል፡፡
በአሁኑ ሰዐት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተቆራረጠ ትምህርት እየሰጡ እንደሚገኙ የተናገሩት ሚኒስትሯ፡ ወጥ የሆነ መማር ማስተማር እንዲኖር ክልሎች እና ከተሞች በትኩረት ሊሠሩ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

በአማራ እና በኦሮሚያ ክልል የሚገኙ ዪንቨርሲቲዎች ከፍተኛ አለመረጋጋት የሚታይባቸው ናቸውም ተብሏል፡፡
በነዚህ ተቋማት ግጭት እንዲከሰት የተጠና ድጋፍ የሚያደርጉ አካላት መኖራቸውንም ፕሮፌሰር ሂሩት አስታውቀዋል፡፡
ምሁራን ለችግሮቹ የመፍትሄ ሀሳብ እንዲያመጡም ተጠይቋል፡፡

አውሎ ሚዲያ ታህሳስ 24/2012 ዓም

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ