ሳልሳይ ወያነ ትግራይ ታሕሳስ 25 እና 26 መስራች ጉባኤ እንደሚያካሂድ ይፋ ኣድርጓል።

0
99

ፓርቲው ዛሬ ለሚዲያዎች በሰጠው ይፋዊ መግለጫ እንዳስታወቀው በሚቀጥሉት ቅዳሜና እሁድ ፖለቲካዊ ፕሮግራሙን በጉባኤተኞች ያስጸድቃል፣ አመራሮቹን ይመርጣል።

ሳልሳይ ወያነ ትግራይ (ሳወት) ብሄራዊ ድርጅት ሆኖ በትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ውስጥ የሚንቀሳቀስ ነው። የትግራይ ህዝብ እያጋጠሙት ያሉት ሁለንተናዊ ችግሮች ጠንካራ ተቋማዊ አሰራር የሚከተልና ሕግና ስርዓት የሚያከብር ብሄራዊ መንግስት ባለመገንባቱ ነው ሲል ፓርቲው ገልፅዋል። ትግራይ ላይ መሰረት ያደረገ ብሄራዊ ፓርቲና የፖለቲካ ፕሮግራም ባለመኖሩ ህዝቡ ራሱን የሚከላከልበትና የሚለማበት ተቋሞችና ስርዓት መገንባት እንዳልቻለ የገለጸው ፓርቲው፣ ይህ ፖለቲካዊ ችግር ለመፍታት እንደተቋቋመ አብስሯል።

ትግራይ ውስጥ አዲስ የፖለቲካ የትግል ባህል እና ነባራዊ ሁኔታዎችን ያገናዘበ ፕሮግራምና ፖሊሲ እናስተዋውቃለን ያለው ፓርቲው የአክሱም ስልጣኔ፣ ከዛ በኋላ የተካሄዱ በጎ የሆኑ ማሕበረሰባዊ እንቅስቃሴዎችና ህዝባዊ ትግሎች እንደ መሰረት ተቀብሎ፣ አዲስ ፍላጎት ላይ የተመሰረተ ትግል እንደሚያካሂድ አስታውቋል።

በተጨማሪም የትግራይ ብሄራዊ ጥቅሞች ብሎ ለለያቸው እንደሚታገል ይፋ ኣድርጓል። በጉባኤው የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የሲቪክ ማሕበራት፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ ታዋቂ ግለሰቦችና ሚዲያዎች ተወካዮች እንደሚገኙም ኣብራርቷል።

አውሎ ሚዲያ ታህሳስ 22/2012 ዓም

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ