ህወሓት ቅዳሜ እና እሁድ “በውህደት” ላይ ውሳኔ ለማሳለፍ ጠቅላላ ጉባኤውን ያካሂዳል፡፡

0
55

በኢህአዴግ መፍረስ እና በውህደት ሀሳብ እንዲሁም በብልፅግና ፓርቲ ምስረታ ላይ በልዩነት የቆመው ህወሓት በጠቅላላ ጉባኤ ውሳኔ ለማሳለፍ እንደሚገደድ ከመሪዎቹ ሲነገር ቆይቷል፡፡

በተለይም ህወሓትን ማፍረስ የሚችለው የህወሓት አባላት እና የትግራይ ህዝብ እንጅ የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ወይም የኢህአዴግ ምክር ቤት አይደለም በሚል ለጠቅላላ ጉባኤ በይደር የተቀመጠ ቀጠሮ መኖሩ ይታወሳል፡፡

ይህንን የመፍረስና አዲስ ፓርቲ የመመስረት ሀሳብ ለማስወሰን ህወሓት ጠቅላላ ጉባኤ ለማድረግ ለቅዳሜ እና ለእሁድ ዝግጅት ላይ መሆኑን ታውቋል፡፡

ባለፉት ሁለት ወራት በኢህአዴግ መፍረስና በብልፅግና ፓርቲ ምስረታ ላይ ከፍተኛ ልዩነት ያሳዩትን የህወሓት አመራሮች ለማነጋገር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ሽማግሌ መላከቻው ይታወሳል፡፡

በተጨማሪም የትግራይ ተወላጅ ባለሀብቶችን ሰብስበው ህወሓት ውህደቱን እንዲቀበል ግፊት እንዲያደርጉ መናገራቸውም የሚታወቅ ነው፡፡

ህወሓት ግን ለመፍረስም ሆነ ለመዋሃድ ተጠቅላላ ጉባኤ ተጠርቶ ውሳኔ እናሳልፋለን በማለት አቋም መያዛቸው የሚታወቅ ነው፡፡

ከሰሞኑ በመቐለ በተካሔደው ኮንፈረስ የፓርቲው ሊቀመንበር ዶክተር ደብረፅዮን ገብረ ሚካኤል የትግራይ ህዝብ እና የህወሓት አባላት ሁኑ ያሉንን ለመሆን ዝግጁ ነን ሲሉ መናገራቸውም ይታወቃል፡፡

ዘጋቢ በቃሉ አላምረው

አውሎ ሚዲያ ታህሳስ 23/2012 ዓ.ም

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ