ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ ከአንጀሊና ጆሊ ጋር ተወያዩ፡፡

0
94

ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ ከፊልም ተዋናይትና በበጎ አድራጎት ስራዎቿ ከምትታወቀው አንጀሊና ጆሊ ጋር ተወያዩ።
አንጀሊና ጆሊ በብሄራዊ ቤተመንግስት ከፕሬዚዳንቷ ጋር በልማት፣ በሴቶች እና በስደተኞች ጉዳይ ላይ የሀሳብ ልውውጥ አድርጋለች።

ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ “የአንጀሊና ጆሊ ጉብኝት ኢትዮጵያ በአስገራሚ የለውጥ ጎዳና ላይ ባለችበትና የሴቶችን ጉዳይ ጨምሮ በሁሉም መስኮች አዲስ ምዕራፍ እየተከፈተ ባለበት ወቅት የተደረገ በመሆኑ ጉብኝቱ ስለ ኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ስለ አፍሪካ ያለውን አተያይና አስተሳሰብ ለመለወጥ የማይናቅ አስተዋፅኦ አለው፡፡” ብለዋል

በሰብአዊ ስራዎቿ የምታወቀው አንጀሊና በበኩሏ “ወደኢትዮጵያ የመጣሁት በህጻናትና ሴቶች እንዲሁም ጤና ላይ መስራት የሚቻልባቸውን እድሎች ለማየት ነው” ብላለች።
ከአንጀሊና ጆሊ ጋር ትውልደ ኢትዮጵያዊቷን የ14 አመት ታዳጊ ዘሃራን ጨምሮ ልጆቿ አብረዋት ተገኝተዋል፡፡

አውሎ ሚዲያ ታህሳስ 21/2012 ዓ.ም

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ