የናይጀሪያና የኮንጎ ዜግነት ያላቸው ሰዎች በአዲስ አባባ ወንጅል እፈፀሙ ነው ተባለ፡፡

0
92

የናይጀሪያና የኮንጎ ዜግነት ያላቸው ሰዎች የማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎችን በመጠቀም በተደራጀ መንገድ በአዲስ አበባ ከተማ የሚፈጽሙት የማታለል ወንጀል እየተበራከተ መሆኑን የኢትዮጵያ ጠቅላይ አቃቤ ሕግ ጽ/ቤት አስታወቀ።

ጽ/ቤቱ በዛሬዉ ዕለት በፌስቡክ ገፁ እንዳሰፈረዉ ማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎችን በመጠቀም በተለይ ሴቶችን በተደራጀ መንገድ የማታለል ወንጀል ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየተበራከተ በመምጣቱ ህብረተሰቡ ጥንቃቄ እንዲያደርግ አሳስቧል።

በጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የተደራጁና ድንበር ተሸጋሪ ወንጀሎች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ፍቃዱ ጸጋ እንደገለጹት ከለፈው ዓመት ነሀሴ ወር ጀምሮ በፌስቡክና በዋትስአፕ ብቻ 40 የሚደርሱ ኢትዮጵያዉያን ሴቶች በዉጭ ሀገር ዜጎች ተጭበርብረዋል።
የናይጀሪያና የኮንጎ ዜግነት ያላቸውና አዲስ አበባ ከተማ ዉስጥ የሚገኙት እነዚህ ተጠርጣሪዎች በፌስቡክ አካውንት በከተማዋ የሚገኙ ሴቶችን ጓደኛ በማደርግና የስልክ ቁጥራቸውን በመለዋወጥ በዋትስ አፕና በፌስቡክ በሚደረጉ የስልክና የቪዲዮ መስተጋብሮች በማጭበርበር ከሴቶቹ ገንዘብ መዉሰዳቸዉን ኃላፊዉ በዝርዝር ገልፀዋል።

በዚህ መንገድ የማጭበርበር ወንጀል የተፈፀመባቸዉን 40 ሰዎችን ጉዳይ ለማየት ሁለት መዝገብ ተከፍቶ ምርመራ መጀመሩንና የናይጀሪያ የኮንጎና የኢትዮጵያ ዜግነት ያላቸዉ 6 ተጠርጣሪዎች መያዛቸዉን አመልክተዋል። በምርመራዉም ሀሰተኛ መታወቂያዎችና የባንክ አካዉንቶች ተገኝተዋል ብለዋል።

ከጠቅላይ አቀቤ ህግ እንድተገኘው መረጃ ተማሳሳይ ወንጀሎች ሊፈጸሙ ስለከሚችሉ ህበረተሰቡ ጥንቃቅ ሊያድርግ ይጋበል፡፡

አውሎ ሚዲያ ታህሳስ 21/2012 ዓ.ም

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ