የኢትዮጵያ የመሬት ምልከታ ሳተላይት የ700 ኪሎ ሜትር ጉዞዋን አጠናቅቃ መረጃ መላክ ጀመረች ተባለ፡፡

0
80

ኢትየጵያ ለመጀመርያ ግዜ የመሬት ምልከታ ሳተላይት ከቻይና ዋና ከተማ ቤይጂንግ 400 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ከሚገኘው የቻይና ሳተላይት ማስወንጨፊያ ጣቢያ ዛሬ ጠዋት 12:21 ደቂቃ ላይ መላኳ ይታወቃል፡፡

ሳተላይቷ ወደታሰበላት ቦታ ደርሳ መረጃ መላክ መጀመሯ ተገልጿል፡፡
ሳተላይቷ ለግብርና፣ ለማዕድን፣ ለአካባቢ ጥበቃ፣ ለአየር ንብረት ለውጥ እና ለመሳሰሉት አገልግሎት መረጃ መስጠት የምትችል ናት፡፡

21 ኢትዮጵያውያን ኢንጅነሮችና ሳይንቲስቶች በፕሮጀክቱ የተሳተፉ ሲሆን እነዚህ ኢትዮጵያውያን ቻይና ውስጥ ባካበቱት እውቀት ወደ ሀገራቸው ሲመለሱ ሙሉ በሙሉ እዚሁ ኢትዮጵያ ውስጥ ሳተላይት ሰርተው ለማምጠቅ እቅድ እንዳላቸው ተናግረዋል።

አውሎ ሚዲያ ታህሳስ 10 /2012 ዓ.ም

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ